የ Dorr በአርትራይተስ ኢንስቲትዩት, ዩናይትድ ስቴትስ
በዚህ ስራችን ላይ እጅግ ትኩረት የምናደርገው በእያንዳንዱ የሕክምና ደረጃ ትኩረት ማድረግ ሲሆን ይህም አንድ ታካሚ ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ከቀዶ ጥገናው በኋላ እስከሚደረግለት ክትትል ድረስ ያካትታል፡ ይህ ቁርጠኝነታችን የታካሚዎችን ደህንነት በመጀመሪያ ደረጃ በማስጠበቅ ቀጥሎ ደግሞ የታካሚዎችን ቀዶ ጥገና ፍላጐት ለምሳሌ በፍጥነት በማገገም፣ አነስተኛ የሆነ የድህረ ቀዶ ጥገና ህመም ፣ የተሻሻለ የጉልበት እንቅስቃሴ እንዲሁም ወደ ጤናማ እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ ማድረግን የመሳሰሉ ፍላጐቶች በማሟላት ታካሚዎቻችን የተሟላ ደስተኛ ህይወት እንዲኖሩ እናግዛቸዋለን፡
ቡምሩንግራድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል በአጥንት መገጣጠሚያ ቅያሪ ቀዶ ጥገና ኤክስፐርት የሆኑት እና የሮቦቱ እጅ የሚታገዝ ቀዶ ጥገና ፈጠራ ባለቤት ከሆኑት ዶ/ር ላውረንስ ዲ ዶር ጋር በመተባበር የሚሰራ ሲሆን የትብብር ስራውም ወደፊት ለታካሚዎቻችን የምንሰጠውን አገልግሎት እንድናሻሽል ስለ አጥንት መገጣጠሚያ ቀዶ ጥገና እውቀትን በመጨበጥ የተሻለ የህክምና አሰጣጥ ዘዴን እንድናዳብር ያደርገናል፡