አንድ ሆስፒታል ስለ ጥናት እና ደህንንት የሚቆረቆር ከሆነ ከሌላ አካል ይህን በተመለከተ ማረጋገጫ ይፈልጋል

የአለም ዓቀፍ የጋራ ኮሚሽን (ጄሲአይ)

ድርጅቱ እውቅና ያገኘው በአለም ዓቀፍ የጋራ ኮሚሽን ነው ቡምሩንግራድ የአሜሪካን ሆስፒታሎችን አረጃጀት በሚመረምረው እና እውቅና የሚሰጠው ድርጅት ክንፍ በሆነው በአለምዓቀፉ የጋራ ኮሚሽን እውቅና የተሰጠው የመጀመሪያው የእስያ ሆስፒታል ነው፡ መስፈርቱ ከ350 ስታንዳርዶች በላይ ያሉት ሲሆን እነዚህ ስታንዳርዶች ከቀዶ ጥገና ንፅህና እስ ማደንዘዣ ቅደም ተከተል እንዲሁም የህክምና ባለሙያዎች እና ነርሶች የትምህርት ደረጃን ያጠቃልላል፡ ጄሲአይ ለሆስፒታሎች በየ 3 ዓቱ የምርመራ ውጤት ይልካል፡

የሆስፒታ የእውቅና ማዕከል

ቡምሩንግራድ በታይላንድ የሆስፒታል እውቅና ካገኙት 800 ሆስፒታሎች የመጀመሪያው ሆስፒታል ሲሆን ከቅርብ ጊዜ በፊት የኤ-ኤችኤ ከፍተኛ የሆስፒታ እውቅና ደረጃኝ ያገ|ኘ ብቸኛ ሆስፒታል ነው

የአለምዓቀፍ የጤና እንክብካቤ እውቅና (ጂኤችኤ)

የጂኤችኤ ስታንዳርዶች ስልታዊ የሆነ እና ምክንያታዊ የሆነ የግምገማ ሂደት መሰረት ሲሆኑ ስታንዳርዶቹም አንድ ድርጅት የህክምና ጉዞ አገልግሎቶችን በተመለከተ ያለውን አያያዝ በተመለከተ ምን አይነት አቀራረብ እንዳለው የሚገመገምበት ነው፡ የጂኤችኤ ስታዳርዶች በመላው የህክምና ጉዞ እንክብካቤ አገልግት ላይ ያለው ቀጣይነት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡ ሰታንዳርዶቹ የተለያዩ የኢኮኖሚ መመዘኛዎች፣ የደንበ|ኞች ፍላጎቶችን፣ የባህል ልዩነቶች እና ለጤና ስርዓቱም ሆነ ለእያንዳንዱ ድርጅት ያለውን የእድገት ደረጃ ከግምት የሚያስገቡ ናቸው፡

ሆስፒታሉ የዓመቱን ምርጥ የህክምና ቱሪዝም ሆስፒታል አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል

ይህ ሽልማት በተለይ ቡምሩንግራድ እና ቫይታል ላይፍ ከአስሩ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን ሽልማቶች ማሸነፋቸው ሆስፒታሉ ለታይላንድ ኩራት ከመሆኑም በተጨማሪ በአለምዓቀፍ ደረጃ ጥራት ያለውን ስታንዳርድ ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡ በ 2018 እ.ኤ.አ ቡምሩንግራንድ ሆስፒታል በእስያ ፓስፊክ የዓመቱ ቁጥር አንድ የህክምና ቱሪዝመ ሆስፒታል የተሰኝ ሲሆን 2018 እ.ኤ.አ ከእስያ ፓስፊክ የጤና እንክብካቤ እና ህክምና ቱሪዝም ኮንፍረንስ እና ሽልማት ዝግጅት ሌሎች ሰባት ሽልማቶችን ይዞ ወደ ሃገር ቤት ተመልሷል

የታይላንድ የ2018 ምርጥ ታማኝ ሆስፒታል

ቡምሩንግራድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል የታይላንድ ምርጥ የቢዝነስ ልህቀት ሽልማትን በ2018 እ.ኤ.አ እጅግ እምነት የሚጣልበት የ2018 ሆስፒታል በሚል ስያሜ በደቡብ ምስራቅ አስያ መጽሄተ ተሸላሚ ሆኗል፡ ይህ ሽልማት የሚሰጠው እጅግ ጉልህ የሆነ ስኬት ላስመዘገበ ተቋም ሲሆን ቡምሩንግራድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታልም በታይላንድ ይህንን እወቅና ያገኘ ብቸናው ሆስፒታል ነው፡

የ2018 ምርጥ ሆስፒታል

ቡምሩንግራድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል-ታይላንድ የ2018 እ.ኤ.አ የእስያ የጤና እንክብካቤ የዓመቱ ምርጥ ሆስፒታል በመባል ሽልማት አግኝቷል የዚህ ዓመት እጩዎች አባይ ባንጊ፣ አጋር ላይፍ ሳይንስ ኤንድ ሄልዝኬር ሊድ፣ ኧርነስት ኤንድ ያንግ፡ ሞሂት ግሮቨር፣ ላይፍ ሳይንስ ኤንድ ኸልዝ ኬር ሊደር፣ ዲሎይት እና ሳብሪና ታይ አጋር እና ምክትል የኢንዱስትሪ መሪ፣ ኸልዝ ኬር አርኤስኤም ሲንጋፖር በተገኙ ዳኞች ተገምግሟል

ለበለጠ መረጃ ወኪሎቻችንን ያናግሩ
ወኪል በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ያለዉን ሕጋዊ ወክላቺን በመጠየቅ ማንኛዉንም አይነት የሆስፒታሉን መረጃ አንዲሁም የጉዞ አና የቀጠሮ አገልግሎትን ያለምን ክፍያ ማግኘት ይችላሉ.ወኪሎቻችን በእርሶ ቃንቃ ስለሚናገሩ እጅግ አርገው ሊረዱዎት ዝግጁ ናቸው